ለማህበር ቤት ለተመዘገቡ news

 የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የ2005 ዓ.ም የ20/80 እና 40/60 የቤት ልማት ተመዝጋቢ ሆነው በማኅበር ተደራጅተው ቤት ለመስራት ቀደም ሲል በኦንላይን የተመዘገቡ አመልካቾች በየሚኖሩበት ወረዳ ቀርበው መረጃቸውን ከየካቲት 16 እስከ መጋቢት 16/2014 ዓ.ም ድረስ በአካል እንዲያረጋግጡ መገለጹ ይታወሳል።

ቢሮው ዛሬ ባወጣው ማስታወቂያ አመልካቾች ምዝገባቸውን የሚያረጋግጡበትን ጊዜ እስከ ሚያዝያ 17 ቀን 2014 ዓ.ም መራዘሙን አስታውቋል።

በዚህም በአዲስ አበባ ከተማ ክልል በራሳችሁም ሆነ በትዳር አጋራችሁ ስም ቤት ወይም የቤት መስሪያ ቦታ የሌላችሁ ወይም ኖሯችሁ ከ1997 ዓ.ም ወዲህ በስጦታ / በሽያጭ ያላስተላለፋችሁ መሆኑን እና ሌሎች መረጃዎችን በቅጽ 01 በማዘጋጀት ምዝገባችሁን እንድታሟሉ ጠይቋል።

ዲያስፖራ ሆነው በኦንላይን የተመዘገቡ የማኅበር ቤት ፈላጊዎች ደግሞ ከመጋቢት 19 ቀን 2014 እስከ ሚያዝያ 17 ቀን 2014 ዓ.ም ባለው ጊዜ ባምቢስ አካባቢ ግሪክ ት/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ 8ኛ ፎቅ ተመዝጋቢዎች ወይም በህጋዊ ወኪሎቻችሁ አማካኝነት በአካል ቀርባችሁ የተዘጋጀውን ቅፅ 001 እንዲሞሉ አስታውቋል።

ከላይ በተጠቀሰው ጊዜ ቀርባችሁ‘ቅፅ -01’ እና ‘ቅፅ- 001’ን ያልሞላችሁ ተመዝጋቢዎች በፈቃዳችሁ የተዋችሁት ተደርጎ እንደሚወሰድ የከተማው ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ገልጿል።

የተሟላ፣ትኩስ እና አስተማማኝ ኮንዶሚንየም እና ሪልስቴት ነክ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.condoaddis.com/ ፌስቡክ፡- https://wwww.facebook.com/condoadis ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/CondominiumforsaleinAddisAbaba1
ቴሌግራም፦ https://t.me/condoaddis በመወዳጀት ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Please follow and like us:
Pin Share

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Translate »
RSS
Follow by Email
Scroll to Top