ለፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የ3ተኛ ዙር የንግድ/ድርጅት ቤቶች ኪራይ ጨረታ ተጫራቾች

ማስታወቂያ

*****
ለፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የ3ተኛ ዙር የንግድ/ድርጅት ቤቶች ኪራይ ጨረታ ተጫራቾች በሙሉ
1. የመጨረሻው የጨረታ አሸናፊዎች ውጤት ይፋ የተደረገ ሲሆን አጠቃላይ ውጤቱም በሁሉም የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችና በዋናው መ/ቤት የውስጥ ማስታወቂያ ሰሌዳ የተለጠፈ በመሆኑ ከ12/07/2014 ዓ.ም. ጀምሮ ለ7 ተከታታይ ቀናት በጨረታ ሒደቱ ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተጫራቾች  በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት የሪከርድና ማህደር አገልግሎት ቢሮ በአካል በመቅረብ  ቅሬታችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

2. የጨረታ አሸናፊዎች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከ12/07/2014 ዓ.ም  ጀምሮ ከአስራ ሁለት ተካታታይ ቀናት በኋላ ባሉት አስር ተከታታይ ቀናቶች ቤቶቹ በሚገኙበት የቅርንጫፍ ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ ውል መዋዋል የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

3. CPO መመለሻ ቀን በተመለከተ ውጤቱ ይፋ ከተደረገበት ከ12/07/2014 ዓ.ም ጀምሮ አስር ተከታታይ ቀናት በኋላ ቤቶቹን በተጫረታችሁባቸው የቅርንጫፍ ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
.
የ 3ኛ ዙር የ157 የንግድ ቤቶች ኪራይ ጨረታ አጠቃላይ ውጤት ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው መተግበሪያ በመግባት የሁሉንም የንግድ ቤቶች ውጤት ማየት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

የመተግበሪያ ሊንክ – http://www.fhc.gov.et:7098/hubd

                     የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን

የተሟላ፣ትኩስ እና አስተማማኝ ኮንዶሚንየም እና ሪልስቴት ነክ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.condoaddis.com/ ፌስቡክ፡- https://wwww.facebook.com/condoadis ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/CondominiumforsaleinAddisAbaba1
ቴሌግራም፦ https://t.me/condoaddis በመወዳጀት ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Please follow and like us:
Pin Share

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Translate »
RSS
Follow by Email
Scroll to Top