አዲስ አበባ የመሬት ይዞታ ስም ዝውውር በ25 ቀጠናዎች ታገደ።

አዲስ አበባ የመሬት ይዞታ ስም ዝውውር በ25 ቀጠናዎች ታገደ።

የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ምዝገባና ማረጋገጫ ኤጀንሲ በከተማዋ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጳጉሜን 5 ቀን 2014 ዓ.ም የካዳስተር ምዝገባ እና እወጃ ሥራ እንደሚካሄድ አስታውቋል።
ከዚህ ቀደም የመሬት ይዞታቸውን በካዳስተር ያላስመዘገቡ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች መረጃዎቻቸውን ለሚቀጥሉት ተከታታይ 15 ቀናት ማዘጋጀት እንደሚችሉ ተነግሯል።
በዚህ ዓመት በመዲናዋ የለሚኩራ ክ/ከተማን ሳይጨምር በ10 ክፍለ ከተሞች ውስጥ በሚገኙ 25 ቀጠናዎች ላይ የመሬት ይዞታን የማረጋገጥ እና የእወጃ ሥራ እንደሚሠራ ገልጿል።
በዚሁ መሰረት ይዞታ የማረጋገጥ እና የእወጃ ሥራው ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2014 ዓ.ም ለ5 ወራት እንደሚሠራ ተመላክቷል፡፡
.
በዚህ ወቅት በሕግ ተይዘው ካሉ የመሬት ጉዳዮች እና የሕግ ክርክሮች ውጪ ምንም ዓይነት የስም ዝውውር አይካሔድም።
FBC
Please follow and like us:
Pin Share

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Translate »
RSS
Follow by Email
Scroll to Top