#የእግድ_መነሳትን_ይመለከታል

#የእግድ_መነሳትን_ይመለከታል
ተቋማችን በመሬትና መሬት ነክ አገልግሎቶች መቆምን በመግለጽ የካቢኔ ውሳኔ ያላቸው እና የመሠረተ ልማት ቅንጅት ስራዎች ከሌሎች ተቋማት ጋር በተቋማቸው አገልግሎት እየሰጠ ያለ በመሆኑ እና በአሁኑ ሰዓት የቆሙ አገልግሎቶች ንፃ ግንባታ ዘርፍ የሚሰጡ በከተማ አስተዳደሩ መሬት ነክ በጊዜያዊነት ታግዶ የነበሩ ውስጥ እገልግሎቶች ለመጀመር፦

1. በሊዝ ይዞታዎች አዲስ የግንባታ ፈቃድ የመስጠት፣ ፕላን ስምምነት፣ የግንባታ ማሻሻያ፣ ለነባር ይዞታ ካርታ ያላቸው በመልሶ ማልማት ውስጥ የተጠናላቸው፣ የሊዝ ይዞታዎች የምትክ ቦታ ከመሬት ሲረጋገጥ የአገልግሎት ክፍያ የመሰብሰብ፣

2. የእድሳት ፈቃድ መስጠት፣

3. የግንባታ ማስጀመሪያ የመስጠት እና የአገልግሎት ክፍያ የመሰብሰብ፣

4. የግንባታ ማስጀመሪያ ወስዶ ክትትል ውስጥ የነበሩ በእርከን የአገልግሎት የመሰብሰብ፣

5. የተለያዩ አካላት የግንባታ መረጃ የመስክ ሪፖርት የመስጠት እና የአገልግሎት ክፍያ የመሰብሰብ

6. የህንፃ መጠቀሚያ ፈቃድ መስጠት እና የአገልግሎት ክፍያ የመሰብሰብ አገልግሎቶች ቢጀመሩ እና ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በከተማ ውስጥ ያለው የውጭ ማስታወቂያ ፈቃድ በአዲስ መልክ የከተማውን በጠበቀ መልኩ ለማዘመን እና በዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ እንቅስቃሴ ላይ በመሆናቸው የውጭ ማስታወቂያ ፍቃድ ለጊዜው አገልግሎት ቢቆም የሚል ሀሳብ በማቅረብ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 6 ያሉት አገልግሎቶች እውቅና ተሰጥቶቸው እንዲጀመሩ በቁጥር ግፈቁ0/1592/2014 ዓ.ም በ 28/3/2014 ዓም በተፈረመ ደብዳቤ መጠየቃችሁ ይታወሳል።

በዚሁ መሰረት በእግዱ ምክንያት የሚቆመውን ልማት እና በህብረተሰቡ ላይ ሊደርስ የሚችለውን እንግልት ታሳቢ በማድረ ከላይ በዝርዝር ለጠየቃችኋቸው አገልግሎቶች እግዱ የተነሳ መሆኑ ታውቆ ህጋዊ መስፈርት መሟላታችው እየተረጋገጠ አገልግሎት እንዲሰጥ እናሳስባለን::

የተሟላ፣ትኩስ እና አስተማማኝ ኮንዶሚንየም እና ሪልስቴት ነክ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.condoaddis.com/ ፌስቡክ፡- https://wwww.facebook.com/condoadis ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/CondominiumforsaleinAddisAbaba1
ቴሌግራም፦ https://t.me/condoaddis በመወዳጀት ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Please follow and like us:
Pin Share

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Translate »
RSS
Follow by Email
Scroll to Top