የ40/60 መኖሪያ ኮንደሚኒየም ቤቶች ቁልፍ ባለ ዕድለኞች ተረከቡ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቤቶች ልማት ፕሮግራም ተገንብተው እጣ የወጣባቸውን የ20/80 እና የ40/60 መኖሪያ ኮንደሚኒየም ቤቶች ቁልፍ ለባለ ዕድለኞች አስረከበ።


የ20/80 ኮንደሚኒየም ቤቶች ተገንብተው ለባለዕድለኞች ሲተላለፉ ይህ ለ13ኛ ጊዜ ሲሆን የ40/60 ኮንደሚኒየም ቤቶች ግንባታ ርክክብ ሥነ-ሥርዓት የተፈጸመው ደግሞ ለ2ኛ ጊዜ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ አመልክቷል፡፡ 
ርክክብ የተፈጸመባቸው ቤቶች “ቱሪስት ሳይት” ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የተገነቡት እንደሆኑም ተጠቅሷል።


“በቱሪስት ሳይት” የተገነቡት ኮንደሚኒየም ቤቶችም ባለ 11 ወለል ፎቅ እንደሆኑና በአጠቃላይ 1 ሺህ 930 ክፍሎች እንዳላቸው ነው የተገለጸው፡፡

በቀጣይም ያላለቁ  ኮንዶሚኒየም ቤቶችን በማጠናቀቅ ለባለቤቶቹ ለማስረከብ  ከተማ አስተዳደሩ እየሠራ መሆኑን የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊዋ ያስሚን ዋህብራቢ ጠቁመዋል፡፡


ኃላፊዋ፥ በአዲስ አበባ የሚስተዋለውን የቤት እጥረት ለመቅረፍም  በአቃቂ  አካባቢ 5 ሺህ ቤቶች የተጀመሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡


ከ12 ሺህ በላይ ቤት ፈላጊ የከተማዋ ነዋሪዎችም በማኅበር መደራጀታቸው የተጠቆመ ሲሆን ከተማ አስተዳደሩ በቀጣይ ችግሩን ለማቃለል እየሠራ መሆንም ተመልክቷል፡፡

FBC
የተሟላ፣ትኩስ እና አስተማማኝ ኮንዶሚንየም እና ሪልስቴት ነክ መረጃዎችን ለማግኘት፡-  

ድረ ገጽ https://www.condoaddis.com/ፌስቡክ፡- https://wwww.facebook.com/condoadisዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/CondominiumforsaleinAddisAbaba1  
ቴሌግራም፦ https://t.me/condoaddis በመወዳጀት ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

የተሟላ፣ትኩስ እና አስተማማኝ ኮንዶሚንየም እና ሪልስቴት ነክ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.condoaddis.com/ ፌስቡክ፡- https://wwww.facebook.com/condoadis ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/CondominiumforsaleinAddisAbaba1
ቴሌግራም፦ https://t.me/condoaddis በመወዳጀት ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Please follow and like us:
Pin Share

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Translate »
RSS
Follow by Email
Scroll to Top