ዜና ለማህበር ቤት የተደራጃችሁ

ለማህበር ቤት የተደራጃችሁ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ በ20/80 እና 40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም ተመዝጋቢ የሆናችሁ እና በጋራ ህንፃ መኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበር ተደራጅታችሁ ቤት ለመገንባት በመመዝገብ በ57 ቡድን ከተደለደላችሁት ውስጥ ቀርባችሁ ሪፖርት ያላደረጋችሁ ተመዝጋቢዎች በሙሉ፡፡

ቀደም ሲል በተቋሙ ማህበራዊ ገፅ በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ ቀርባችሁ ሪፖርት እንድታደርጉ ጥሪ ቢተላለፍም እሰከአሁን ቀርባችሁ ሪፖርት ያላደረጋችሁ በመኖራችሁ ለመጨረሻ ጊዜ በ25/7/2015 – 27/7/2015 ድረስ ለ 3 ተከታታይ የሥራ ቀን ባምቢስ ከግሪክ ት/ት/ቤት አጠገብ በሚገኘው የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ቢ.ቁ.601 ቀርባችሁ ሪፖርት ካላደረጋችሁ በገዛ ፍቃዳችሁ ከቡድን ድልድሉ የተሰረዛችሁ መሆኑን እና በምትካችሁ ተጠባባቂዎችን የምንተካ መሆኑን እናሣውቃለን፡፡

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ

በገጻችን የምናቀርባቸውን የቤቶች ልማት ኤጀንሲ መረጃዎች በአማራጭነት በቴሌግራም ቻናላችን ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ።
👇👇👇👇👇
t.me/condoaddis

ተጨማሪ ለመረዳት
👇👇👇
www.condoaddis.com/03042023-1

Please follow and like us:
Pin Share

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Translate »
RSS
Follow by Email
Scroll to Top