ማስታወቂያ በ20/80 እና 40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም ተመዝጋቢ ሆናችሁ

ማስታወቂያ

ቀደም ሲል በ20/80 እና 40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም ተመዝጋቢ ሆናችሁ ነገር ግን በጋራ ህንጻ መኖ/ቤ/ህ/ሥራ ማህበር በመደራጀት ቤት ለመገንባት በወጣው ማስታወቂያ በonline መመዝገባችሁ ይታወሳል፡፡

ይሁን እንጂ ከወረዳ አስፈላጊውን መረጃ በወቅቱ ማሟላት ባለመቻላችሁ በተደጋጋሚ የእንመዝገብ ጥያቄ ስታቀርቡ ቆይታችኋል፡፡

ስለሆነም በጎደሉ ማህበራት ማሟያ እና ተጠባባቂ መያዝ ስለተፈለገ ከመጪው ሰኞ 28/09/15 ጀምሮ እስከ 2/10/15 ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ባምቢስ በሚገኘው የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 601 እየቀረባችሁ እንድትመዘገቡ እናሳውቃለን፡፡

በቀጣይ የግንባታውን 70% ጊዜ በአጭር ጊዜ ውስጥ በቁጠባ ደብተራችሁ የማስገባት ግዴታ እንዳለባችሁ አውቃችሁ እንድትዘጋጁ እያሳሰብን፡፡
ለምዝገባ ሲመጡ ይዘው የሚያቀርቧቸው መረጃዎች፡-

1. የአዲስ አበባ ነዋሪ የሆነና የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፤

2. ትውልደ ኢትዮጵዊ ሆኖ ዜግነት የቀየረ ከሆነ የሚኖርበት ሀገር ፓስፖርት ነገር ግን ዜግነቱን ካልቀየረ ደግሞ የመኖሪያ ፈቃድና ፓስፖርት፤

3. ያላገባ ከሆነ 6 ወር ያላለፈው ያላገባ የሚል ማስረጃ እና የፈታ ከሆነም የፈታ መሆኑን ማስረጃ፤

4. ያገባ ከሆነ የጋብቻ ማስረጃ፤

5. ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ በተመዝጋቢውም ሆነ በትዳር አጋሩ ስም ቤትም ሆነ ቤት መስሪያ ቦታ አለመኖሩን ማረጋገጫ ደብዳቤ፤

6. ለመደራጀት የሚመጣው ተወካይ ከሆነ ህጋዊ ውክልና፤

7. በ2005 ዓ.ም ምዝገባ ያደረገና የቁጣባ ሂሳብ ደብተሩን ያልዘጋ፤

ለበለጠ መረጃ በስ.ቁ 0115553820 መደወል የምትችሉ መሆኑን ቢሮው ያሳውቃል፡፡

የአዲስ አበባ የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ

http://www.aahdab.gov.et

https://t.me/aahdabofficial

https://www.facebook.com/aahdabofficial

Please follow and like us:
Pin Share

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Translate »
RSS
Follow by Email
Scroll to Top