የኮንዶሚንየም እድለኞች ውል የማዋዋል ሂደት ለ30 የስራ ቀናት ተራዘመ

የ14ኛ ዙር የ20/80 እና የ3ኛ ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት እድለኞች ውል የማዋዋል ሂደት ለ30 የስራ ቀናት ተራዘመት

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በ14ኛ ዙር የ20/80 እና 3ኛ ዙር የ40 /60 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን እጣ አውጥቶ ለባለ እድለኞች ለማስተላለፍ ከጥር 1 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ መጋቢት 26/2015 ዓ.ም ውል ሲያዋውል መቆየቱ ይታወቃል :: የመወያያ ጊዜውም መጋቢት 26/2015 ዓ.ም. ተጠናቋል፡፡ ይሁን እንጂ ባለፉት 60 የስራ ቀናት አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታዎችን በማጠናቀቅ መዋዋል ካለባቸው 25,773 መካከል ውል የተዋዋሉት 1,835 ብቻ በመሆናቸው ቀሪዎቹ በፍርድ ቤት፣ በግዳጅ ፣ በወሊድና በሌሎችም ምክንያቶች ቀርበው መዋዋል ላልቻሉ ውል እንዲዋዋሉ ለማድረግ እና ፕሮሰስ ጀምረው ያላጠናቀቁትን እንዲያጠናቅቁ ለማስቻል ኮርፖሬሽኑ በአዋጅ ቁጥር 64//2011 አንቀፅ 22 ንኡስ አንቀጽ 2 መሰረት እስካሁን ውል ያልተዋዋሉ የቤት እድለኞችን ማዋዋል እንዲያስችል ከመጋቢት 27/2015 ዓ.ም ጀምሮ 30 የስራ ቀናት ያራዘመ መሆኑን እያሳወቅን በነዚህ ቀሪ ቀናት ውስጥ ቀርቦ ያልተዋዋለ ማንኛውም የቤት እድለኛ ቤቱን እንዳልፈለገው ተቆጥሩ ለኮርፖሬሽኑ ተመላሽ የሚደረግ መሆኑን እንዲያውቁት ለማሳሰብ እንወዳለን ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ

ለተጨማሪ መረጃ 👇👇
Fb.me/condoadis

ወይም

T.me/condoaddis

Please follow and like us:
Pin Share

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Translate »
RSS
Follow by Email
Scroll to Top