ማስታወቂያ ለ20/80 እና 40/60 ዕድለኞች

ማስታወቂያ ለ20/80 እና ለ40/60 እድለኞች

በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በ20/80 (ለ14 ኛ ጊዜ) እና በ40/60 (ለ3ኛ ጊዜ) ባለፈው ሕዳር ወር 2015 ዓ.ም. የጋራ መኖሪያ ቤቶችን እጣ ማውጣቱ ይታወቃል። በዚህ መሰረት የጋራ መኖሪያቤት እድለኞች ከጥር 1 ቀን /2015 ዓ.ም. ጀምሮ መገናኛ በሚገኘው በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ግቢ ውስጥ የኮርፖሬሽኑ የአንድ ማእከል አገልግሎት መስጫ ውስጥ ውል ማዋዋል ስለሚጀመር በሁለቱም የቤት ልማት መርሀ-ግብር ባለድለኞች በአካል እየተገኛችሁ እንድትዋዋሉ እያሳሰብን የውል ማዋዋሉ ፕሮግራም ለ60 የስራ ቀናት ወይም ለሁለት ወር ብቻ የሚቆይ እንደሆነ እያሳወቅን ተዋዋዬች ማሟላት የሚገባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች በአንድ ማእከል የአገልግሎቱ መስጫ የምታገኙ ሲሆን በተጨማሪም በቢሮና በኮርፖሬሽኑ ዌብሳይት እና በሌሎች ማህበራዊ ሚዲያዎች የተለቀቀ https://t.me/condoaddis  መሆኑን እያሳወቅን በተሰጠው ጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርቦ ያልተዋዋለ እድለኛ በመመሪ ቁጥር 3.3/2011 መሰረት ቤቱን እንዳልፈለጉት ተቆጥሮ ተመላሽ እንደሚደረግ ከወዲሁ ለማሳወቅ እንወዳለን ፡፡

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን

ታህሳስ 28/2015 ዓ.ም.
_____________
በገጻችን የምናቀርባቸውን መረጃዎች በአማራጭነት በቴሌግራም ቻናላችን ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ።
👇👇👇👇👇
t.me/condoaddis
እንዲሁም፦
Fb.me/condoadis

Please follow and like us:
Pin Share

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Translate »
RSS
Follow by Email
Scroll to Top