በ20/80 14ኛ ዙር በ40/ 60 3ኛ ዙር የቤት ባለ እድለኞች ውል የማዋዋል ስራ ዛሬጥረ 1/2015 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2፡ 00 ሰአት ጀምሮ

በአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፓሬሸ‍እን በ20/80 14ኛ ዙር በ40/ 60 3ኛ ዙር የቤት ባለ እድለኞች ውል የማዋዋል ስራ ዛሬጥረ 1/2015 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2፡ 00 ሰአት ጀምሮ ኮርፓሬሽኑ ባለ እድለኞችን እየመዘገበ ቅፅ ዜሮ ዘጠኝን (09) ሲሰጥ ውሏል ።

በዛሬው እለት ብቻ በ20/80 እና በ40/60 በጥቅሉ 2667 ሰዎች ተመዝግበው ቅፅ 09 ኝን መውሰድ ችለዋል።

የቤቶች ልማት ኮርፓሬሽኑ አሁን ካለው የተመዝጋቢ ሁኔታ መጨናነቅን ለማስቀረት እና ፈጣን አገልግሎት መስጠት እንዲያስችለው የማወያያ ቀን መርሀግብር አውጥቷል ። በዚህ መሰረት የቤት ባለ እድለኞች መጀመሪያ መገናኛ ቦሌ ክፍለ ከተማ ውስጥከሚገኘው የአንድ ማእከል አገልግሎት መስጫ ማእከል በመቅረብ ተመዝግበው ቅፅ 09 ኝን መውሰድ አለባቸው ። ቅፁን ከወሰዱ በኃላ ወደ መኖሪያ መንደራቸው ቀበሌ አስተዳደር ወስደው ቅፁን አስሞልተው እንደ ታሸገ ወደ ውል መወያያ አንድ ማእከል ሳይከፍቱ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል ። ስለሆነም ባለ እድለኞች ገና ለሁለት ወር ይቆያል ብለው እንዳይዘናጉ ቢያንስ ቅፅ 09 ኝን በዚህ ሶስትና አራት ቀን ውስጥ አምጥተው ካስረከቡ በኃላ በወጣው የማወያያ መርሀግብር መሰረት እየቀረቡ መዋዋል ይጠበቅባቸዋል ።

ለተጨማሪ👇
www.condoaddis.com

Please follow and like us:
Pin Share

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Translate »
RSS
Follow by Email
Scroll to Top