የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት እስከ ምሽቱ 1 ሰዓት ድረስ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ይፋ አደርጓል።

#እንድታውቁት
(የካቲት 1,2016 ጀምሮ)

የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት እስከ ምሽቱ 1 ሰዓት ድረስ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ይፋ አደርጓል።

በተደረገው የስራ ሰዓት ማሻሻያ መሰረት ከዛሬ የካቲት 1 ጀምሮ ፦

– ከሰኞ እስከ አርብ ከጥዋቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ #ምሽቱ 1:00 ሰዓት ድረስ (በአዲስ አበባ ዋናው መ/ቤት እና በድሬዳዋ ቅርንጫፍ) አገልግሎት ይሰጣል።

👉 እስከ ምሽት 1:00 ሰዓት የሚቆየው የስራ ሰዓት በሌሎች ቅርንጫፎችም በሂደት እንደሚጀመር ተነግሯል።

– ቅዳሜ ከጥዋት አንስቶ እስከ ቀኑ 11:30 ድረስ (በሁሉም ቅርንጫፍ) #አገልግሎት ይሰጣል።

በአዲሱ የስራ ሰዓት ማሻሻያ አገልግሎቱ ” ለምሳ ሰዓት ” በሚል የማይቋረጥ ሲሆን በምሳ ሰዓትም አገልግሎት ማግኘት ይቻላል ተብሏል።

ከዚህ ቀደም በዚህ መስሪያ ቤት አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው ከጥዋት 3:00 ሰዓት አንስቶ ሲሆን ለምሳ ተብሎ ደግሞ ሰራተኞቹ ወጥተው 8:00 ነበር የሚገቡት።

ቅዳሜ ደግሞ ግማሽ ቀን ነበር የሚሰራው።

ከዛሬ በኃላ በአ/አ ዋናው መ/ቤት እና በድሬዳዋ ቅርንጫፍ ከሰኞ እስከ አርብ ከጥዋት 2:00 ሰዓት እስከ ምሽት 1:00 ሰዓት ፤ ቅዳሜ በሁሉም ቅርንጫፍ ከጥዋት እስከ 11:30 አገልግሎት ይሰጣል።

👇 Read more
condoaddis.com

Please follow and like us:
Pin Share

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Translate »
RSS
Follow by Email
Scroll to Top