የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ለ3ኛ ዙር የ40/60 እና 14ኛ ዙር 20/80 ባለእድለኞች

 

የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ለ3ኛ ዙር የ40/60 እና 14ኛ ዙር 20/80 ባለእድለኞች

እስከ ግንቦት 7 አጠናቁ

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በ14ተኛው ዙር የ20/80 እና በ3ተኛው ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ዕጣ አውጥቶ ለባለ ዕድለኞች ለማሰተላለፍ ከጥር 1 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ መጋቢት 26/2015ዓ.ም ለ60 የስራ ቀናት ውል ሲያዋውል መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ በተሰጣቸው ጊዜ ውስጥ በተለያየ ምክንያት ቀርበው ውል መዋዋል ላልቻለ እንዲዋዋሉ _ ለማድረግ እና ፕሮሰስ ጀምረው ያላጠናቀቁትን እንዲያጠናቅቁ ለማስቻል ኮርፖሬሽኑ በአዋጅ ቁጥር 64/2011 አንቀፅ 22 ንዑስ አንቀፅ 2 መሰረት እስካሁን ውል ያልተዋዋሉ የቤት ዕድለኞችን ማዋዋል እንዲያስችል ከመጋቢት 27/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለ30 የስራ ቀናት ያራዘመ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ሆኖም በተሰጠው ጊዜ ውስጥ ቀርባችሁ ውል ያልተዋዋላችሁ የቤት ዕድለኞች የውል ጊዜው የሚጠናቀቀው ግንቦት 7/2015 ዓ.ም በመሆኑ በቀረው ቀን ውስጥ ቀርባችሁ ውላችሁን እንድትፈፅሙ እያሳሰብን ይህ ሳይሆን ቀርቶ በቀሪ ቀናት ውስጥ ቀርቦ ያልተዋዋለ ማንኛውም የቤት ዕድለኛ ቤቱን እንዳልፈለገው ተቆጥሮ ለኮርፖሬሽኑ ተመላሽ የሚደረግ መሆኑን እንዲያውቁት እናሳስባለን፡፡

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት

Please follow and like us:
Pin Share

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Translate »
RSS
Follow by Email
Scroll to Top