ማስታወቂያ በአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ በጋራ ህንጻ ኅ/ስ/ማህ/ ለመደራጀት ቀደም ሲል በኦን ላይን ለተመዘገባችሁ በሙሉ

ማስታወቂያ

በአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ በጋራ ህንጻ ኅ/ስ/ማህ/ ለመደራጀት ቀደም ሲል በኦን ላይን ለተመዘገባችሁ በሙሉ

የአዲስ አበባ ከተማ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ በ2005 ዓ.ም. በ20/80 እና በ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም ተመዝጋቢዎችን በጋራ ህንጻ መኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበር የቤት ተጠቃሚ ለማድረግ በወጣው መመሪያ ቁጥር 1/2013 መሰረት በጋራ ህንፃ መኖሪያ ቤት ህ/ሥራ ማህበር በፈቃደኝነት አደራጅቶ የቤት ተጠቃሚ ለማድረግ በኦን ላይን መመዝገባችን ይታወቃል፡፡

በዚህም መሠረት ቢሮው አስፈላጊውን የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ሲስራ ቆይቶ በኦን ላይን የተመዝገቡትን በየሚኖሩበት ወረዳ እና በአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና እተዳደር ቢሮ አስፈላጊውን ጥሪ በማድረግ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ በአካል ቀርበው የሚፈለግባቸውን መረጃ ያሟሉትን ተመዝጋቢዎች በ57 ቡድን በመደልደል በማህበራዊ ሚዲያ የፌስቡክና የቴሌግራም አድራሻችን የለቀቅን መሆኑን እየገለጽን፣

1. አብሮ የመደራጀት ፍላጎት ያላቸውን እድል ለመስጠት ሲባል፡-

👉እርስ በርስ የቡድን መቀያየር የሚፈቀደው በተመሣሣይ የህንፃ ከፍታ እና የቤት አይነት ብቻ ይሆናል።

👉ቅይይሩ የሚፈጸመው በሁለቱ ተስማሚ ተመዝጋቢዎች በአካል ቀርበው ወይም ህጋዊ ውክልና ባላቸው ሠዎች ብቻ ተፈፃሚ ይደረጋል፡፡

👉ሁለቱ ተስማሚዎች ያቀረብነውን ቅፅ ሞልተው የታደሠ መታወቂያ ኮፒ ይዘው ከ08/05/15 እስከ 22/5/15 ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ብቻ ከደንበል ወደ ባንቢስ በሚወስደው መንገድ ግሪክ ት/ቤት አጠገብ በሚገኘው የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቤት ማህበራት አደረጃጀት ክትትል ዳይሬክቶሬት 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 601 እየቀረቡ የሚስተናገዱ ይሆናል፡፡

2. የተጓደሉ የየቡድን አባላትንና ተጠባባቂዎችን ምዝገባ በተመለከተ፡-

👉 ከዚህ በፊት በጋራ ህንጻ መኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበራት ተደራጅቶ ቤት ለመገንባት በኦንላይን ተመዝግባችሁ ነገር ግን ከወረዳ አስፈላጊውን መረጃ ሣታሟሉ የቀራችሁ አሁን ለመደራጀት ፍላጎቱ ያላችሁ የሚጠበቅባችሁን መረጃ ከወረዳ ቤቶች አስ/ጽ/ቤት ቀርባችሁ በማሟላት ከ08/05/15 እስከ 15/5/15 ለተከታታይ 5 የሥራ ቀናት ውስጥ ብቻ በመቅረብ እስፈላጊውን እንድታሟሉ፣

👉ምዝገባው ሲጠናቀቅም የተጓደሉ የየቡድን አባላትንና ተጠባባቂዎችን በእጣ የምንለይ ይሆናል፡፡

ማሳሰቢያ

1. ከዚህ በኋለ የሚኖሩ ስራዎች የእርስ በርስ የቡድን አባላት እንዲተዋወቁ ለማድረግ እና የማደራጀቱ ሥራ በህብረት ስራ ማህበራት ኤጀንሲ በኩል ስለቀጣዩ የማደራጀት መርሃ ግብር የሚገለፅ ይሆናል።

2. በ20/80 እና በ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም ተመዝግባችሁ በመረጃ ቋት ስማችሁ የሚገኝና በተከፈተላችሁ የባንክ ሂሳብ ገንዘብ በመቆጠብ ላይ ያላችሁ ቤት ፈላጊዎች ከዚህ በፊት በኦንላይን ሣትመዘገቡ የቀራችሁ ነገር ግን በጋራ ህንፃ የቤት ማህበራት ተደራጅቶ ቤት ለመገንባት የምትፈልጉ በቅርቡ ምዝገባ ስለምናደርግ ማስታወቂያውን እንድትከታተሉ እናሣውቃለን፡፡

Please follow and like us:
Pin Share

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Translate »
RSS
Follow by Email
Scroll to Top