የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ለምስራቅ አፍሪካ

🔴 የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ለምስራቅ አፍሪካ ኢንቨስትመንት እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ የናይሮቢ ሰነድ መዋዕለ ነዋይ ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍራንክ ሊዮድ ዊቲ ገለጹ።

የናይሮቢ ሰነድ መዋዕለ ነዋይ ገበያ በኬንያ የሚገኝ ከ60 ዓመታት በላይ አገልግሎት እየሰጠ ያለ የአፍሪካ የሰነድ መዋዕለ-ነዋይ ገበያ ነው።
ገበያው በአፍሪካና በኬንያ ኢንቨስትመንት ለማሳለጥ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገራት ኢንቨስተሮች አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

ተቋሙ ከኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ጋር በትብብር የመሥራት ፍላጎት እንዳለውም ገልጿል።
የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ፍራንክ ሊዮድ ዊቲ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፉን ለውጭ ባለኃብቶች ክፍት ለማድረግ እያከናወነች ያለው ተግባር የሚበረታታ ነው።
ይህም እርምጃ ለሀገሪቱ ምጣኔ ኃብት እድገት ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳለው ነው ያብራሩት።
በተለይም ኢትዮጵያ የካፒታል ገበያን በማቋቋምና የራሷ የሰነድ መዋለ ነዋይ ገበያ እንዲኖራት እያከናወነች ያለው ተግባር አዲስ የፋይናንስ ምህዳር እንደሚፈጥር ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በፋይናንስ ዘርፍ እያከናወነች ያለው ለውጥ በምስራቅ አፍሪካ በምጣኔ ኃብት ዘርፍ ያላትን የስበት ማዕከልነት የሚያጸናና ለቀጣናው እድገትም አዎንታዊ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል

ከዚህ ባለፈ በተለይም የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ በቀጠናው ለሚሰሩ መሰረተ ልማቶች የፋይናንስ ምንጭ ሆኖ ሊያገለግል እንደሚችልም ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
ተቋሙ ከኢትዮጵያ የካፒታል ገበያና ከሌሎች ተዋናዮች ጋር ስትራቴጂክ አጋርነትን በመፍጠር የመሥራት ፍላጎት እንዳለው ጠቁመዋል።

ET securities

Please follow and like us:
Pin Share

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Translate »
RSS
Follow by Email
Scroll to Top