የጋራ መኖሪያ ንግድ ቤት ጨረታ ያሸናፉ ተጫራቾች ውል የማዋዋል ሂደት ተጀመረ

የጋራ መኖሪያ ንግድ ቤት ጨረታ ያሸናፉ ተጫራቾች ውል የማዋዋል ሂደት ተጀመረ

.
በ2015 በጀት ለጨረታ የቀረቡ የ4ኛው ዙር 40/60 የጋራ መኖሪያ ንግድ ቤቶችን ያሸነፉ ተጫራቾች ውል የማዋዋል ሂደት በይፋ ተጀመረ፡፡ የውል ማዋዋል ሂደቱ እስከ ጥር 25 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ እንደሚካሄድም ተጠቁሟል፡፡
.
የጋራ መኖሪያ ንግድ ቤት ጨረታ አስተዳደር ቡድን መሪ ወ/ሮ ዘይነባ መሐመድ በሰጡት ማብራሪያ ጨረታ ከጥር 3 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ከአንድ ወር በላይ ሲካሄድ የቆየው አራተኛው ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ንግድ ቤት አሸናፊ ተጫራቾች ቦሌ ክፍለ ከተማ በሚገኘው በአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን አንድ ማዕከል አገልግሎት ያሸነፉባቸውን የንግድ ቤቶች ውል የማዋል ሂደት በይፋ መጀመሩን ገልፀዋል፡፡
.
የንግድ ቤቶቹ በለሚ ኩራ፣ አዲስ ከተማ፣ ልደታ እና አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተሞች በተለይ በሀያት፣ ሰሚት፣ ሰንጋ ተራ፣ ቱሪስት እና በሌሎችም ሳይቶች ውስጥ እንደተገነቡ የገለፁት ወ/ሮ ዘይነባ በተካሄደው ጨረታ 2,333 ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸውንም አስረድተዋል፡፡
.
በጨረታው አሸናፊ የሆኑት ተጫራቾች ውል ለመዋዋል በሚመጡበት ወቅት የታደሰ መታወቂያ፣ ያገቡ ወይም ያላገቡ መሆናቸውን የሚያመለክት የጋብቻ ሁኔታ ማስረጃ፣ የንግድ ቤት መለያ ቁጥር እና አራት ፎቶግራፍ አሟልተው በመገኘት በወጣላቸው መርሃግብር መሠረት ቀርበው የንግድ ቤት ውል መፈፀም እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝዋል፡፡
.
የአራተኛው ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ንግድ ቤት የጨረታ ውል እስከ መጪው ሚያዝያ 25 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ የሚካሄድ መሆኑን የጠቆሙት ቡድን መሪዋ በጨረታ ያሸነፉ ተወዳዳሪዎች በወጣው መርሃግብር መሠረት ቀርበው ውል ያልፈፀሙ ከሆነ በመመሪያው መሠረት በተጠባባቂነት ለተያዙ ሌሎች ተወዳዳሪዎች የንግድ ቤቶቹ የሚተላለፉ በመሆኑ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች በወቅቱ ቀርበው ውል እንዲፈፅሙ አሳስበዋል፡፡
or here ——> www.t.me/condoaddis.com
Please follow and like us:
Pin Share

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Translate »
RSS
Follow by Email
Scroll to Top