ማስታወቂያ በ70/30 በጋራ ህንፃ መኖሪያ ቤት ህ/ሥራ ማህበር ለመደራጀት ላመለከታችሁ

በ20/80 እና በ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም ተመዝጋቢ ሆነው የቤት ተጠቃሚ ለመሆን በመጠባበቅ ላይ የሚገኙትን በ70/30 በጋራ ህንፃ መኖሪያ ቤት ህ/ሥራ ማህበር በፈቃደኝነት አደራጅቶ የቤት ተጠቃሚ ለማድረግ በመመሪያ ቁጥር 1/2013 መሠረት ፈላጊዎችን በኦንላይን መመዝገባቸው ይታወቃል፡፡

በዚሁ መሠረት ቀደም ሲል ተመዝግባችሁ ለተጠባባቂነት እጣ በወጣላችሁ ቅደም ተከተል መሠረት ስማችሁ በዚህ ማስታወቂያ ላይ የወጣ ሲሆን ተመዝጋቢዎች ከ13/09/2016 እስከ 19/09/2016 ከዘህ በታች የተዘረዘሩትን ቅድመ ሁኔታዎች በሟሟላት እና ለተመዘገባችሁበት የቤት አይነት የሚከፈለውን የገንዘብ መጠን በቀድሞ የ20/80 ወይም 40/60 ቁጠባ አካውንት ለይ ገቢ በማድረግ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ብቻ በቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የጋራ መኖሪያ እና ቤት ህብረት ስራ ማህበራት ዳይሬክቶሬት ዘውትር በስራ ሰአት 6ኛ ፎቅ በመቅረብ ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳስባለን፡፡

ተመዝጋቢዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መረጃዎች ለምዝገባ በሚመጡበት ጊዜ አሟልተው እንዲመጡ እና ይዘው በመቅረብ እንዲመዘገቡ እናሳስባለን፡፡

1. ቅጽ 01 /ቢሮ በመቅረብ የሚወሰድና በወረዳ ቤቶች ጽ/ቤት በኩል ተሞልቶ የሚመለስ/

2. የጋብቻ ሁኔታ ማስረጃ፡- ያገባ ከሆነ የትዳር አጋር የታደሰ መታወቂያ፣ ያላገባ ከሆነ 6 ወር ያልሞላው / ኦርጅናል እና ኮፒ/

3. የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ /ዲያስፖራ ከሆነ ፓስፖርት/ ኦርጅናል እና ኮፒ/

4. የ20/80 ወይም የ40/60 ቤት ተመዝጋቢ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ/ኦርጅናል እና ኮፒ/

5. የባንክ ደብተር ፎቶ ባለበትና የመጨረሻ ገቢ በተደረገበት ገጽ በኩል ኮፒ ተደርጎ/ኦርጅናል እና ኮፒ/

6. ተወካይ ከሆነ የውክልናውን ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን

የስም ዝርዝሩን ያግኙ 👇👇

የማህበር_ቤት_ተጠባባቂዎች_ሰም_ዝርዝር1

Please follow and like us:
Pin Share

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Translate »
RSS
Follow by Email
Scroll to Top