በ2005 ዓ.ም. በ20/80 እና በ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም ተመዝጋቢዎች

 

በ2005 ዓ.ም. በ20/80 እና በ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም ተመዝጋቢዎች

የአዲስ አበባ ከተማ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ በ2005 ዓ.ም. በ20/80 እና በ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም ተመዝጋቢዎችን  በጋራ ህንፃ መኖሪያ ቤት ህ/ሥራ ማህበር በማደራጀት  የቤት ተጠቃሚ ለማድረግ  በመመዝገብ የሚጠበቅባቸውን መረጃ ያሟሉ  4518 ግለሰቦች በ57 ቡድን መደልደልደላቸው የሚታወቅ ነው።

በመሆኑም በቡድን ከተደለደላችሁት ውስጥ  ከዚህ በታች ስማችሁ የተጠቀሰ የማህበር ቤት ተመዝጋቢዎች ከባንክ ባገኘነው መረጃ መሰረት  የ20/80 እና የ40/60 ፕሮግራም ቁጠባችሁን ያቋረጣችሁ መሆኑ ስለተረጋገጠ ከተደለደላችሁበት ቡድን የምትሰረዙ መሆኑን አውቃችሁ  ሆኖም ግን ቅሬታ ካላችሁ ቅሬታችሁን ከየካቲት 15/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

አድራሻችን ከደንበል ወደ ባንቢስ በሚወስደው መንገድ ግሪክ ት/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሲሆን ለቤት ልማትና ፋይናንስ አቅርቦት ዳይሬክቶሬት 7ኛ ፎቅ  ቢሮ ቁጥር  704 እየመጣችሁ ቅሬታችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ቅሬታ ያለው ተመዝጋቢ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቅሬታውን ካላቀረበ ከድልድሉ የሚሰረዝ መሆኑን እና በምትኩ ተጠባባቂ እንደሚተካ ለማሳወቅ እንወዳለን።

ማሳሰቢያ ፦

ቁጠባችሁን ያላቋረጣችሁ በቅረቡ ወደ ስራ ስለሚገባ የሚጠበቅባችሁን 70  በመቶ ለመቆጠብ ዝግጅት እያደረጋችሁ እንድትጠብቁ እናሳስባለን፡፡

Please follow and like us:
Pin Share

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Translate »
RSS
Follow by Email
Scroll to Top