የጋራ መኖሪያ ቤቶች የንግድ ሱቆች ጨረታ ወጣ

የጋራ መኖሪያ ቤቶች የንግድ ሱቆች ጨረታ ወጣ

5ኛው ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ የንግድ ሱቆች ጨረታ ሰነድ ከ19/09/15 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 28 የስራ ቀናት መሸጥ ይጀምራል

በ40/60 ፕሮግራም በተለያዩ ክ/ከተሞች ያስገነባቸውን 3310 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሕንፃ ላይ የሚገኙ ንግድ ቤቶችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ ይፈልጋል ::

ኮርፖሬሽኑ ለሽያጭ ያቀረባቸውን የንግድ ቤቶች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ተወዳድሮ ለመግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ድርጅት በኮርፖሬሽኑ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከግንቦት 17/2015 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ሰኔ 19/2015 ዓ.ም. ባሉት 28 የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 10፡30 ድረስ ፣ ቅዳሜ ግማሽ ቀንን ጨምሮ እስከ 6 ሰዓት ድረስ በአካል በመቅረብና የማይመለስ ብር 400 በመክፈል ከታች በተዘረዘሩት የጨረታ ሰነድ መሸጫ ስፍራዎች መግዛት ይችላሉ፡፡

የጨረታ ሳጥን ሰኔ 19/2015 ከምሽቱ 11 ሰዓት ተዘግቶ በማግስቱ ሰኔ20/2015 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡00ሰዓት ተጫራጮች በተገኙበት ይከፈታል፡፡

ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎችን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የጨረታ ሰነድ መሸጫ ቦታዎች

1. አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ቤቶች ጽ/ቤት 1ኛ ፎቅ

2. ሰንጋ ተራ 40/60 ቤቶች ብሎክ 4

3. የካ ክ/ከተማ ቤቶች ጽ/ቤት 4ኛ ፎቅ 4 አራዳ ክ/ ከተማ ግቢ ውስጥ ግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ቢሮ ቁ/G03

5. 40/60 ቦሌ ቡልቡላ ቅርንጫፍ 1 ጽ/ቤት 6 40/60 አያት 49 ማዞርያ ብሎክ 21 ቅርንጫፍ 2 ጽ/ቤት

ስልክ
011-8 12-23-82
0118 -62-57-15
_____________________
👇👇👇👇👇
t.me/condoaddis
እንዲሁም፦
Fb.me/condoadis

Please follow and like us:
Pin Share

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Translate »
RSS
Follow by Email
Scroll to Top