የመጀመሪያ ዙር የማህበር ቤት ተጠባባቂዎች ዳግም ምዝገባ እስከሚቀጥለው ሰኞ መራዘሙ ተገለፀ

የመጀመሪያ ዙር የማህበር ቤት ተጠባባቂዎች ዳግም ምዝገባ እስከሚቀጥለው ሰኞ መራዘሙ ተገለፀ

የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ በከተማዋ የሚስተዋለውን የመኖሪያ ቤት እጥረት ለመፍታት ከሚከተላቸው አማራጮች መካከል የማህበር ቤት ግንባታ አንዱ ነዉ።

በዚህም መሰረት ቢሮዉ ፍላጎት እና አቅሙ ያላቸውን  የ20/80 እና የ40/60 የቤት ልማት ተመዝጋቢዎችን በህብረት ሥራ ማህበር ማደራጀቱ የሚታወቅ ነዉ።

በመሆኑም ከዚህ ቀደም ሲደረጁ ተጠባባቂ የነበሩ የመጀመሪያ ዙር ተመዝጋቢዎች ለማደራጀት አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታዎችን እና ዶክመንቶችን አሟልተው ለቀረቡ ተጠባባቂ ግለሰቦች ለተከታታይ አምስት ቀናት ዳግም ምዝገባ ሲያካሂድ የቆየ ሲሆንና ትላንት ቢጠናቀቅም ነገር ግን መረጃ ሳይደርሳቸው ቆይተው  ተንጠባጥበው እየመጡ ያሉ ተመዝጋቢዎች በመኖራቸው እስከ ቀጣይ ሰኞ ማለት አስከ 26/09/16 ዓ.ም ድረስ መራዘሙን የቢሮው የማህበር ቤት ዳይሬክቶሬት ገልጿል።

ለሁለተኛ ዙር ተጠባባቂዎችንም በቀጣይ ምዝገባ እንደሚካሄድ ቢሮው ገልጿል።

Please follow and like us:
Pin Share

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Translate »
RSS
Follow by Email
Scroll to Top