የኢትዮጲያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ለካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች ፈቃድ የሚሰጥበትን መመሪያ  ወደ ስራ አሳወቀ፡፡


የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች ፈቃድ አሰጣጥና ቁጥጥር መመሪያ ቁጥር 980/2016’’  ጥር 9 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በይፋ ስራ ላይ መዋሉን የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ዛሬ ባዎጣው መግለጫ አስታውቋል።

የኢትዮጲያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ለካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች ፈቃድ የሚሰጥበትን መመሪያ  ወደ ስራ ማስገባቱን አስታውቋል።

ባለስልጣኑ መመሪያውን ለህዝብ ይፋ አድርጎ ለውይይት ካቀረበ ከሁለት ወራት ቡሃላ ነው ወደ ስራ ማስገባቱን ያስታወቀው።

ይህ መመሪያ በሃገራችን የካፒታል ገበያን ለማስጀመር ወሳኝ ምዕራፍ ሲሆን ገበያው ተዓማኒ እና ፍትሐዊ መሆኑን ለማረጋገጥ የሚረዳ እና የኢንቨስተሮችን ጥበቃ የሚያጎለብት የሕግ ማዕቀፍ ይሆናል።
ሲሉ የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ታዬ ገልጸዋል።

በዚህ ማዕቀፍ ውስጥ 15 የተለያዩ የፈቃድ ዓይነቶች ይኖራሉ። እነዚህ ፈቃዶች የሚሰጡት በመመሪያው ላይ የተዘረዘሩትን ቅድመ ሁኔታዎች ለሚያሟሉ አመልካቾች ሲሆን ባለሥልጣኑ እነዚህን አገልግሎት ሰጪዎች የሚቆጣጠር ይሆናል።

✳️ ሙሉ መግለጫው ካላይ  ተያይዟል።
✳️ የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች ፈቃድ አሰጣጥና ቁጥጥር መመሪያ ቁጥር 980/2016’’ ከታች አያይዘናል
⏬⏬⏬⏬⏬⏬
Et Securities Market
ስልክ፡  +251913587955
ቴሌግራም      t.me/etstock
ፌስ ቡክ፡   https://fb.me/Etstock
Linkedin(ሊንክዲን):https://www.linkedin.com/company/etstock/

✳️ የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች ፈቃድ አሰጣጥና ቁጥጥር መመሪያ ቁጥር 980/2016
Procedur-Amharic-version-latest

Please follow and like us:
Pin Share

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Translate »
RSS
Follow by Email
Scroll to Top