ለመሆኑ Crowdfunding ምንድነው?

👉Crowdfunding…

የኢትዮጵያ የመዋእለ-ነዋይ ገበያ /Ethiopian Capital Market Authority/ የመዋእለ-ነዋይ ገበያው ሲጀመር ፈቃድ እንደሚሰጣቸው ከዘረዘራቸው የገበያ ተዋናዮች መ ካከል Crowd funding አንዱ ነው።

ለመሆኑ Crowdfunding ምንድነው?

Equity Crowdfunding አዲስ ወደ ንግድ ለሚገቡ /Startups/ አሊያም ለጀማሪ ኩባንያዎች የካፒታል ማሰባሰቢያ ዘዴ ነው።

Crowd የሚለው ቃል “ብዝሐ” በሚለው የሚወከል ሲሆን ለብዙሀኑ በትንሽ ገንዘብ አክሲዮን በመሸጥ ካፒታል የሚሰበሰብበት ዘዴ ነው። እያንዳንዱ ኢንቨስተር ባዋጣው ገንዘብ እኩሌታ አክሲዮን ይሰጠዋል፣ የትርፍ ድርሻ ተካፋይም ይሆናል።

ከEquity Crowdfunding ሌላ ግለሰቦችን ለመርዳት እንዲሁም ለመሸለም የሚደረጉ የCrowdfunding ዓይነቶችም አሉ። (ለምሳሌ Gofundme)

ይህ ገንዘብ ትንንሽ ብሮችን ኢንቨስት ከሚያደርገው ብዙሀን የሚሰበሰበው በቴክኖሎጂ በታጀበ የኦንላይን ስርዓት ሲሆን እያንዳንዱ ሰው በገዛው አክሲዮን ልክ ወዲያውኑ ኢ-ሰርተፊኬት ያገኛል። ድርሻውን መሸጥ ሲፈልግም በቀላሉ በኦንላይን ሽጦ መውጣት ይችላል።
——–
Tilahun G.

 

Please follow and like us:
Pin Share

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Translate »
RSS
Follow by Email
Scroll to Top