ኢ.ሰ.መ.ገ የባለአክሲዮኖች ድልድል እያደረገ ነው

የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ባለአክሲዮኖች ምን አይነት መብት እንደሚኖራቸው የሚወስን ድልድል አያደረገ ነው።

ከ48 የኢትዮጵያ እና የውጭ ሀገር ተቋማት 1.5 ቢሊዮን ብር ካፒታል ያሰባሰበው የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ የኢንቨስተሮቹን የድርሻ ድልድል በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ዶይቸ ቨለ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ሰነደ-ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ቺፍ ኦፕሬቲንግ ኦፊሰር ሚካኤል ሐብቴ “አሁን የድርሻ ድልድል እያደረግን ነው። ገና አልተጠናቀቀም” ሲሉ ተናግረዋል። በዚህ ሣምንት ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቀው ሒደት በኩባንያው ድርሻ የገዙ ባለ አክሲዮኖች ምን አይነት መብት እንደሚኖራቸው የሚወስን ነው ተብሏል።

ከካፒታል ገበያው ድርሻ ከገዙ ሦስት የውጪ ሀገር ኢንቨስተሮች አንዱ የሆነው የናይጄሪያው ኤክስቼንጅ ግሩፕ፤ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ቴሚ ፖፖላ የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ የቦርድ አባል እንደሚሆኑ ተገልጿል።

ከኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ 25 በመቶው ድርሻ የመንግሥት ሲሆን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እና 4 የመንግሥት ተቋማት ለ25 በመቶው ድርሻ 225 ሚሊዮን ብር ከፍለዋል። የተቀረው 75 በመቶ ድርሻ በሀገር ውስጥ የግል ዘርፍ እና የውጭ ባለሀብቶች መያዙ ነው የተገለፀው።

ለተጨማሪ 👇
ETStocks

Please follow and like us:
Pin Share

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Translate »
RSS
Follow by Email
Scroll to Top