ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ወደ የኢትዮጵያ ሴኩሪቲስ ልውውጥ (Ethiopian Securities Exchange (ESX))

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የ50 ሚሊዮን ብር ኢንቨስትመንት ወደ የኢትዮጵያ ሴኩሪቲስ ልውውጥ (Ethiopian Securities Exchange (ESX)) በማድረግ ሶስትኛው የፋይናንስ ተቋም ለመሆን ችሏል።

መዓዛ ወንድሙ የግሎባል ባንክ የኮርፖሬት ስትራቴጂና ትራንስፎርሜሽን ዋና መኮንን የካፒታል ገበያ የኢኮኖሚ እድገትን ለማምጣት ለሚደረግ  ሂደት ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ጠቅሰዋል።

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያን ለማስፋትና ለማሳደግ ESX በአጠቃላይ 625 ሚሊዮን ብር ከድርጅቶችና ተቋማት ለመሰብሰብ እየሰራ ይገኛል። እስካሁን ድረስ የዚህን ሩብ መጠን ያሰባሰበ ሲሆን ይህም ከሶስቱ ባንኮች 147.5 ሚሊዮን ብር ኢንቨስትመንት ማግኘት ችሉዋል። ከመንግስት የኢንቨስትመንት ቀኝ እጅ ከሆነው EIH ስር ከሚተዳደሩ ድርጅቶች ደግሞ 275 ሚሊዮን ብር ማግኘቱ አይዘነጋም።

ዘመን ባንክ በቀዳሚነት ከፋይናንሰ ተቋማት የመጀመሪያው በመሆን ባሳልፍነው የጥር ወር አምስት በመቶ ድርሻ ለመዉስድ 47.5 ሚሊየን ብር ኢንቨስት አድርጓል፡፡ በመቀጠል ስንቄ ባንክ በያዝነው ወር በ50 ሚልየን ብር ኢንቨስትመንት ከአምስት በመቶ ትንሽ ከፍ ያል ድርሻ ለመያዝ ችሏል፡፡

ዶክተር ጥላሁን የESX ዋና ሃላፊ እንዳሉትም የግሎባል ባንክ ተሳትፎን አድንቀው እንደዚህ ያሉ ከግሉ ዘርፍ የሚደረጉ ድጋፎች ESX የያዘውን የኢትዮጵያ ፋይናንስ ስርዓት ላይ ስር ነቀል ለውጥ የማምጣት አርዳታ ያደርጋል ብለዋል።

የ ፌስቡክ page https://www.fb.com/etstocks
የ ቴሌግራም page https://t.me/etstocks

Please follow and like us:
Pin Share

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Translate »
RSS
Follow by Email
Scroll to Top